የህዝብ ተወካዪች ምክር ቤት በነገው እለት ይሰበሰባል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ነገ ጥቅምት 08 ቀን 2011 ዓ.ም በሚያካሂደው 3ኛ መደበኛ ስብሰባው፤

አጀንዳዎች፤

1. የም/ቤቱን 4ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣

2. የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና

ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ማጽደቅ፣

3. የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤ መምረጥ፣

4. ጠ/ሚ/ር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በምክር ቤቱ ተገኝተው የመንግስታቸውን አቋም ለምክር ቤቱ እንዲሚያሰሙ ይጠበቃል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here