– ደቻቱ ለረዢም ጊዜ ገንደ መርሻ ይባል ነበር
( እስክንድር ከበደ)

በ19ኛው ክፍለዘመን ጅልዴሳ በሀረርና በቀይ ባህር ዳርቻ መካከል የነበረው የንግድ መስመር ወሳኝ ጣቢያ ሆና አገልግላለች። ደብሊዩ ሲ ቤከር የተባሉ ጸሃፊ እ ኤ አ በ1842 በጻፉት ጽሁፍ ጀልዴሳ በዘይላ እና ሀረር ካራቫን የሲራራ ነጋዴዎች የንግድ ጉዞ ውስጥ ማረፊያ ጣቢያ ነበረች።

ጽሃፊው በ1886 ጣሊያናዊው ፔትሮ ፖሮ በአካባቢው ሰዎች በደፈጣ መገደሉን ዳግማዊ ምንሊክ ሃረርን ለማጥቃት በምክንያትነት ይጠቀሳሉ።ጀልዴሳ በዘመኑ የኢትዮጵያ መንግስት የአካባቢ አስተዳደሪ መቀመጫ ነበረች።የድሬደዋ መቆርቆርና የአዲስ አበባ -ድሬደዋ ባቡር መስመር መዘርጋት የጀልዴሳን ጠቀሜታ እንዳሳጣት ይነገራል።

አቶ መርሻ ናሁሰናይ እ ኤ እ 1890ዎቹ እና ድሬደዋ ስትቆረቆር (1902 ) አስተዳዳሪ በመሆን አገልግለዋል።

በኢትዮ ሶማሊያ ጦርነት ወቅት የሱማሌ ወታደሮች ድሬ ደዋን ለመቆጣጠር ጀልዴሳን በመያዝ ወደ ከተማዋ ቀርበው ነበር። የኢትዮጵያ ጦር ዘጠነኛው ክፍለጦር ከኩባ የታንክና ከባድ መሳሪያ አሃድ ጋር በመተባበር ጀልዴሳን በየካቲት 1970 መልሶ ይዞል።

እ ኤ አ በ2008 የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ጥምር ግብረ ሃይል አባላት ለአገልግሎት ከመረጡት ሰባት የኢትዮጵያ አካባቢዎች አንደኛዋ ጀልዴሳ ነበረች።

አሜሪካኑ ከኢትዮጵያ የእንስሳት ህክምና ባለሙያዎች ጋር በመሆን ከ20ሺህ በላይ የቀንድ ከብቶችን ከልዩ ልዩ የከብቶች በሽታዎች ለመከላከል ክትባት የስጡባት ከተማ ናት።

In 2008, the United States of America selected Jaldessa as one of seven locations where servicemen of the Combined Joint Task Force-Horn of Africa worked with Ethiopian veterinarians to vaccinate more than 20,000 animals: cattle were inoculated against blackleg and anthrax, while sheep and goats were inoculated against contagious caprine pleuro-pneumonia and peste des petits ruminants.

(Ambassador Joins CJTF-HOA Team to Promote Ethiopian Livestock Health)

በሐረር ከተማ ለጥቂት ዓመታት ከኖሩና በከተማዋ የፀጥታ (ፖሊስ) ሃይል ኃላፊ ሆነው ካገለገሉ በኋላ ጄልዴሳ የምትባለው ታሪካዊ ከተማና አካባቢዋ አስተዳደሪ ሆነው ተሾሙ።

በዚያን ጊዜ ግን ሽዋንና የተቀሩትን የኢትዮጵያ ክፍሎች ከቀይ ባሕርና ከገልፍ ኦፍ ኤደን (Gulf of Aden) ጋር ያገናኝ የነበረው የካራቫን (caravan) ንግድ መተላለፊያ በር ነበረች። የጉምሩክ መቀመጫም ነበረች። ስለሆነም አቶ መርሻ ስትራቴጂክ ቦታን የማስተዳደር ልዩ ኃላፊነት ተጥሎባቸው ነበር።

አንዳንድ መረጃዎች የሚጠቁሙት ደግሞ ከኢትዮጵያ የድንበር ክልል እስከ አዋሽ ድረስ ያለውን አካባቢ በሙሉ ይቆጣጠሩ እንደነበር ነው። በተለይም በድንበር እና አካባቢዎች ጥበቃ ረገድ ከፍተኛ ድርሻን አበርክተዋል።

ከጄልዴሳ አስተዳዳሪነታቸው በፊት የሐረር ፖሊስ ኃላፊ ሆነው ማገልገላቸው ለፀጥታው ሥራ እንዳዘጋጃቸው ይታመናል።

ከጅቡቲ የተነሳው የባቡር ሀዲድ እ.ኤ.አ. በ1902 ዛሬ ድሬዳዋ ካለችበት ቦታ ሲደርስ በአቶ መርሻና በፈረንሳዊው ሌዎን ሸፍነ መሪነት አዲስ ከተማ እንዲቆረቆር ትእዛዝ ተሰጠ።

የቦታውም ስም መጀመሪያ አዲስ ሐረር ተባለና ትንሽ ቆይቶ ግን ድሬዳዋ የሚል ስያሜ ተሰጠው። በዚያው ዓመት አቶ መርሻ የድሬዳዋና አካባቢው የመጀመሪያ አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ።

ብዙም ሳይቆይ በምድር ባቡር ኩባንያው ባልደረቦችና በበርካታ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ድካም ድሬዳዋ ቶሎ ቶሎ መገንባት ጀመረች። በአጭር ጊዜ ውስጥም ዘመናዊ የሆነ ከተማ ተቋቋመ።

አቶ መርሻ በከተማውና አካባቢው አስተዳዳሪነት እስከ 1906 እ.ኤ.አ. ድረስ ካገለገሉ በኋላ ለሚቀጥሉት ሃያ ዓመታት ማለትም ጡረታ እስከወጡብት ጊዜ ድረስ የኢሳ ግዛቶች እና የባቡር ሀዲዱ ጥበቃ ሀይል ኃላፊ በመሆን ሰርተዋል። በልጅ ኢያሱ ዘመነ ስልጣን ለአጭር ጊዜ ተሽረው የነበረ ሲሆን ኢያሱ ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ወደ ቦታቸው መመለሳቸውን የታሪክ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

አቶ መርሻ ናሁሰናይ ከሠላሣ ዓመታት በላይ ሀገራቸውን በተለያዩ መስኮች አገልግለዋል። አንደኛ በዓፄ ምኒልክና ራስ መኮንን መሪነት ሐረርና አካባቢዋ ወደ ኢትዮጵያ ከተቀላቀሉ በኋላ በአካባቢው ፀጥታና መረጋጋት እንዲኖር አግዘዋል። ሁለተኛ ከተሞችን በማስተዳደር ረገድ በተለይም የድሬዳዋ ከተማ እንድትቆረቆርና እንድታድግ ልዩ ድርሻ አበርክተዋል።

በዚህም ምክንያት ደቻቱ የሚባለው ቦታ ለረጅም ጊዜ ገንደ መርሻ እየተባለ በአካባቢው ነዋሪዎች ይጠራ ነበር። አቶ መርሻ ዘመናዊ ስልጣኔ ማለትም ዘመናዊ ሀሣቦች፣ ዘመናዊ የአስተዳደር ዘዴዎች እና የቴክኖሎጂ ውጤቶች (የምድር ባቡርና የመሳሰሉትን) ወደ ሀገር እንዲገቡ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

ዘመናዊነት ማለት ደግሞ አውሮፓዊ መሆን ሳይሆን ከውጭው ዓለም የሚገኘውን ዕውቀት ተሞክሮና ድጋፍ ለሀገር እድገትና ህዝባዊ ጥቅም የሚውሉባቸውን መንገዶች መፈለግና ተግባራዊ ማድረግ እንደሆነ ከተረዱት አንዱ ነበሩ።

አቶ መርሻ ኢትዮጵያ ከውጭው አለም ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ እንዲሁም የንግድና ኢኮኖሚ ግንኙነት ማጠናከር ነበር። አቶ መርሻ በዚህም መስክ ልዩ አስተዋፅዖ አድርገዋል።

በተለይም ከአድዋ ድል በኋላ የአውሮጳ የአሜሪካና የሌሎች ሀገሮች መንግስታት የኢትዮጵያን ነፃነትና ሉዓላዊነት ለመቀበል መወሰናቸው ለዘመናት ሲጠበቅ የነበረውን ስልጣኔ ለማስገባት አመቺ ሁኔታን በመፍጠሩ በርካታ ዲፕሎማቶች፤ ጋዜጠኞችና ሳይንቲስቶች፤ ፀሀፊዎችና ቱሪስቶች ኢትዮጵያን ጎበኙ።

አቶ መርሻ የጄልዴሳ ጉምሩክ ኃላፊ ስለነበሩ ወደ ሀገሪቱ የሚወጣውንና የሚገባውን ሁሉ በበላይነት ይቆጣጠሩ ነበር። ሸቀጦች ዘይላ በተባለው የብሪትሽ ሶማሌላንድ ወደብና በጅቡቲ (ፍሬንች ሶማሌላንድ) በኩል እንደልብ ይገቡና ይወጡ ስለነበር ከተማዋ በንግዱ ዓለም ታዋቂ ሆና ነበር።

ለምሣሌ ኢትዮጵያና እንግሊዝ (ብሪታንያ) በ1897 እ.ኤ.አ. በፈረሙት ዲፕሎማሲያዊ ውል አንቀጽ ሦስት መሠረት ጄልዴሳ ለሁለቱም ሀገሮች ንግድ ክፍት እንድትሆን ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር።

የካራቫን ነጋዴዎች እና መንገደኞች ጄልዴሳ ሲደርሱ ከሀገር ውጭ ያመጧቸውን ግመሎችና በቅሎዎች ወደመጡብት ሰደው ለቀጣዩ ሀገር ውስጥ ጉዟቸው የሚይስፈልጓቸውን እንሰሳት ከአካባቢው ነዋሪዎች እንዲከራዩ ይደረግ ነበር። ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ዕቃ ቀረጥ እንዲከፈልበት ስለተደረገም ለመንግስት ከፍተኛ የገቢ ምንጭም ሆኖ ነበር።

ኢትዮጵያ በጊዜው እንደ ቡና፤ የእንሰሳት ቆዳ፤ ከብት፤ የዝሆን ጥርሶችና የመሳሳሉትን ሸቀጦች ወደተለያዩ የአፍሪቃ፤ እስያ፤ መካከለኛው ምሥራቅና አውሮጳ ሀገሮች በኤደን በኩል ትልክ ነበር። በተለይም የጅቡቲ ወደብ መከፈት ለጄልዴሳ ጉምሩክ መጠናከርና ለንግድ መስፋፋት ከፍተኛ እርዳታ አድርጓል፡ አቶ መርሻም ወደ ጁቡቲ ለሥራ ይሄዱ ነበር።

በ1902 እ.ኤ.አ ድሬዳዋ ስትቆረቆር የከተማውና አካባቢዋ አስተዳዳሪና የድሬዳዋ ጉምሩክ የመጀመሪያው ኃላፊ ሆኑ።

በ1894 እ.ኤ.አ ዓጼ ምኒልክ የምድር ባቡር ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ ከተስማሙ በኋላ የቅርብ አማካሪዎቻቸው የሆኑት የስዊሱ ተወላጅ አልፍሬድ ኢልግ (Alfred Ilg: 1854-1916) እና ፈረንሳዊው ሌዎን ሸፍነ (Leon Chefneux: 1853- 1927) ለሀዲዱ ግንባታ ሥራ የሚያስፈልገውን መሰናዶ ጀመሩ።

የምድር ባቡር ኩባንያም በአስቸኳይ ተቋቋመ። የባቡር ሃዲዱ ሥራ በ1897 እ.ኤ.አ ሲጀመር አቶ መርሻ ከኢትዮጵያ በኩል በበላይነት እንዲቆጣጠሩ በምኒልክ አደራ ተጣለባቸው።

ለዚህም ኃላፊነት የበቁት የባቡር ሀዲዱ የሚይልፍባቸው ቦታዎችና ህዝቦች አስተዳዳሪ በመሆናቸው ብቻ ሳይሆን የፈረንሳይኛ ቋንቋን ጠንቅቀው ስላጠኑና ሰለውጭው ዓለምም ሰፊ ዕውቀት ስለነበራቸውም ጭምር ነበር።

የተለያዩ የታሪክ ሙህራን ጽሁፎች የባቡር ሀዲዱን የዘመኑ ትልቅ የቴክኖሎጂ ውጤት ብለው ጠርተውታል።የምድር ባቡር ወደ ኢትዮጵያ መግባት በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ኢኮኖሚያና ማህበራዊ ለውጥን አስከትልዋል።

በጅቡቲ በኩል ሸቀጥ ወደተለያዩ ሀገሮች ከድሮው በበለጠ ፍጥነት በባቡር ለማስወጣትና ለማስገባት በመቻሉ ንግድ እንዲጠናከር ረድቷል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የኑሮ ደረጃ በፊት ከነበረው በጣም አድጓል። በርካታ መንደሮችና ከተሞች በባቡር ሀዲዱ ምክንያት ተቋቁመዋል።

የህዝብ ከቦታ ቦታ መዘዋወርም ጨምሯል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የሀዲዱ መዘርጋት ከረጅም ጊዜ መጠራጠርና ቸልታ በኋላ አውሮፓውያኖች በኢትዮጵያ ላይ ኢንቨስትመንት መጀመራቸውን ያመለክታል።

የአቶ መርሻ አርአያነትና ሀገራዊ ውለታ በእርግጥ አልተረሳም። በድሬዳዋ ከተማ በዓፄ ኃይለሥላሴ በስማቸው መንገድ ተሰይሞላቸው እስካሁን ድረስ አለ። ድሬዳዋ የተመሠረትችበትን 105ኛ ዓመት በቅርቡ ስታከብር ስማቸው ተጠርቶ ተመስግነዋል። ከዚራ የሚገኝ መንገድ በስማቸውም ይጠራል።

ከሁሉም በላይ ጅልዴሳን የሃላ ታሪክ ማየት የኢትዮጵያን ጥንታዊ ንግድና ህዝቦች ትስስር የሚነገረን
ቁምነገር አይጠፋውም ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here