በቀድሞ ጊዜ በቴሌቪዥን የስፖርት ዝግጅት ሲጀምር የሚታዩ ምስሎች መካከል

የፋጡማ ሮባ ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ የሚያሳየው ምስል በጊዜው የነበረ ያስታውሰዋል ።

እኤአ በ1996 ኣትላንታ ላይ ኃይላት በ10 ሺህ ወርቁን ሲያመጣ፤

ጌጤ በ10 ሺህ ነሃሱ የኛ ነው ስትል ፤በማራቶን ሴቶች ፋጡማ ፈርቀዳጃ ድል ኣስመዝግባ ጮቤ ኣስረግጣለች ።

ከኣትላንታ አንድ ዓመት በፊት 1995 እኤአ ስዊድን ላይ በኣለም ሻምፒዮና

ሀገራን ወክላ ተሳታፊ ብትሆን 19 ደረጃ ይዛ ኣጠናቃለች ።

በቀጣይ ዓመትም ኦሎምፒክን እንድትሳተፍ የሚያደርግ ድል በጣልያን የሮም ማራቶን ኣሸንፋ

ጉዞ ወደ ኣትላንታ በማቅናት አይረሴውንና ታሪካዊውን ድል ኣሳየችን ።

ከዛ ቀጥሎ ባሉ ዓመታትም ከ1997 እስከ 1999 ድረስ በቦስተን ማራቶን

ለሶስት ተከታታይ ዓመት በማሸነፍ ኣጃይብ ኣስብላለች ፋጡማ ሮባ ።

የከተማው ሰው “our lady” የእኛ እምቤት እያለ ይጠራታል።

የኦሎምፒክ ድሏበኢትዮጵያና በኣፍሪካ የሴቶች ማራቶን ቀዳሚ ያደርጋታል።

የእርሷን የኦሉምፒክ ድል በማራቶን ከ16 ዓመት በኃላ ቲኪ ገላና ለንደን ላይ ኣስገኝታልናለች።

በኣጠቃላይ በኦሉምፒክ በ በሴቶች ማራቶን ሁለት ወርቅ የሜዳልያ አለን ።

በኣለም ሁለት ኣገሮች ብቻ ናቸው ሁለት ወርቅ በሴቶች ማራቶን ያላቸው ኢትዮጵያና ጃፓን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here