በሰኔ 16 ቀን 2010 ዓም በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት ተጠርጥረው በማረፊያ ቤት በሚገኙት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ተጨማሪ ሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደኃላፊነት ከመጡ በኋላ ለተመዘገበው ለውጥ ድጋፍ ለመስጠት በተጠራው ሰልፍ ላይ በተፈጸመው ጥቃት በማቀነባበር በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ አቶ ተስፋዬ ላይ ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ ይገኛል።

ፖሊስ ቀሪ ምርመራ ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የሰባት ቀናት ጊዜ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ ተረኛ ችሎት ፈቅዶለታል።

ተጠርጣሪው ጉዳያቸው በአፋጣኝ እንዲታይላቸው በመጠየቅ የፍርድ ሂደቱ እየተጓተተ እንደሆነ በመግለጽ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤቱ አሰምተዋል።

በዚህ መሰረት ፖሊስ በአቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ የሚያደርገውን ምርመራ በማጠናቀቅ ክስ ለመመስረት የሚያስችለው የምርመራ ውጤት ለመስከረም 24 ይዞ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here