በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራውን ከፍተኛ የባለስልጣናት ልዑክ አቀባበል ለማድረግ መዘጋጀቱን ፌዴራል ፓሊስ አስታወቀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘይኑ ጀማል፥

ከአቀባበል ስነስርዓቱ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት የሁከት እና ጸጥታ ችግር እንዳይገጥም

ከ1 ሺህ በላይ ወጣቶች በጸጥታ ማስከበር ተግባሩ ላይ ይሳተፋሉ ብለዋል።

ኮሚሽነሩ ህብረተሰቡ በሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባው የድጋፍ ሰልፍ ያሳየውን ስርዓት መድገም እንዳበት ያሳሰቡ ሲሆን፥

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከወጣቶች ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡

በሰኔ 16 የድጋፍ ያጋጠመው ችግር ለአዲሱ አመራር ትምህርት የሰጠ መሆኑንና

ህብረተሰቡ ስነ ስርዓቱን ለማበላሸት ፍላጎት ያለው አካል በተመለከተ ጊዜ በአፋጣኝ ለፖሊስ እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አጠራጣሪ ተግባራትን በሚመለከትበት ወቅት ማንኛውም አካል በስልክ ቁጥር
09-44-70-37-45
09-12-33-72-00
09-44-05-46-80
09-11-60-80-24 እንዲያሳውቅ ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርባዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ለመቀበል ዝግጅት ማድረጉን ፌዴራል ፓሊስ ገለፀ

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ለመቀበል ዝግጅት ማድረጉን ፌዴራል ፓሊስ ገለፀ

Posted by FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) on Friday, July 13, 2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here