ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባለፈው መስከረም በአዲስ አበባ የተፈረመውን የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ለማብሰር በተዘጋጀው ስነስርዓት ላይ ለመሳተፍ ወደ ጁባ ተጓዙ።

ፕሬዝዳንቷ ጁባ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲትን ጨምሮ የደቡብ ሱዳን መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በጁባ ጆን ጋራንግ አደባባይ በሚካሄደው ስነስርዓት ላይ የደቡብ ሱዳን መንግሥትና ተፋላሚ ኃይሎች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን የተለያዩ ሀገራት መሪዎችም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚሁ ስነስርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የዑጋንዳ፣ የሱዳን፣ የኬንያ እና የሌሎች ሀገራት መሪዎችና ተወካዮች ንግግር ያደርጋሉ።

ምንጭ፡- የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here