በምዕራብ ጎጃም ዞን በጃቢ ጠህናን ወረዳ ፈተገም ድግት ቀበሌ ልዩ ቦታው ገልሜ ልዩ ግራር እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ/ም ይህ ወንጀል ይፈጸማል፡፡

በግምት ከሌሊቱ በ8፡00 ሰዓት አካባቢ የግል ተበዳይ የአቶ ፀጋዬ ስንታየሁ የሆኑት ከታሰሩበት ሁለት በሬዎች ይጠፉታል፡፡

በሬዎች መጥፋታቸውን ሲመለከቱ በአካባቢው የድረሱልኝ ድምፅ ያሰማሉ፡፡

ህብረተሰቡ ሊኖሩ ይችላሉ በተባለ ቦታ ሁሉ መፈለግ ይዘዋል፡፡

በቀን 17-02-2011 ዓ/ም በፍኖተ ሰላም ከተማ ቀበሌ 02 በተለምዶ አባ ሻንቆ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ከብቶች ታርደው

በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1-16813 በሆነች ባጃጅ ስጋውን ሊጭኑ ሲሞክሩ

ለፍለጋ በወጡ አካላትና በፀጥታ ሃይል ትብብር ሲደረስባቸው በወቅቱ ወንጀለኞቹ ሩጠው ያመልጣሉ፡፡

ፖሊስና ማህበረሰቡ ባደረጉት ብርቱ ክትትል ተከሳሽ የሆኑት

1ኛ ተስፋየ ታገለ ማርቆስ

2ኛ መንግስቱ በላይ እንየው

3ኛ አበጀ/ባሪያው/ስሜነህ አራጋው ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን በተፋጠነ በማጣራትና አጠናቋል፡፡

የምርመራ መዝገቡን በ/RTD/እንዲታይ ለጃቢ ጠህናን ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት መዝገቡን በመላክ በተከሳሽች ላይ ክስ ተማሰረተ፡፡

የጃቢ ጠህናን ወረዳ ፍርድ ቤት መዝገቡን በመመርመር የግራ ቀኝ ማስረጃወችን በማዳመጥ ተከሳሾች ተከላከሉ ተብለው ቢፈቀድላቸውም የአቃቢ ህግ ማስረጃወች መቃወም ባለመቻላቸው በቀን 27-02-2011 ዓ/ም በጃቢ ጠህናን የባህል አዳራሽ ህዝቡ ባለበት ችሎት በማዘጋጀት ፍርድ ቤቱ

1ኛ በተስፋየ ታገለ ማርቆስ ላይ በ7 ዓመት ጽኑ እስራትና በ7000/ሰባት ሽህ ብር/ መቀጫ

2ኛ በመንግስቱ በላይ እንየው በ6ዓመት ጽኑ እስራትና በ3000/በሦስት ሽህ ብር/መቀጫ

3ኛ አበጀ/ባሪያው/ስሜነህ አረጋ በተባለው በ6ዓመት ጽኑ እስራትና በ1500/በአንድ ሽህ አምስት መቶ ብር/ ወስኖባቸዋል፡፡

በችሎት የነበሩ ሰዎች በፍርድ ቤት የተበየነባቸውን ቅጣት አስመልክተው  በሰጡት አስተያየት የህግ የበላይነት የተረጋገጠበትና ፍትሃዊ ውሳኔ ሲሆን የሰውን ንብረት በሃቅ ያፈራውን የአርሶ አደሩን ህይወት የሆነውን በሬ ወስዶ ማረድ ለልኳንዳ መሸጥ የትም አያደርስም ፡፡

አርሶአደሩም ቢሆን ሃብትና ንብረቱን በተገቢው መንገድ በመጠበቅ አጥፊ ካሉ ቀድሞ መረጃ ለፀጥታ ሃይሉ በመጠቅም ሰላማችንን መጠበቅ ይኖርብናል፡፡

የህግ የበላይነት እንዲከበር እና አጥፊወች እንዲጠየቁ ላደረጋችሁ በሙሉ ምስጋናችን የላቀ ነው ፡፡ወንጀልን በጋራ እንከላከል  ማለታቸውን የምዕራብ ጎጃም ፖሊስ ዘግቧል፡፡

West Gojjam Zone police/ ፖሊስ/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here