የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር የ2010 የግማሽ ዓመት ሪፖርት ላይ እንደገለጸው ድርጅቱ ለነዚህ 120 አውቶብሶች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ አልቻለም፡፡

ዋና ኦዲተሩ ባደረገው የኦዲት ማጣራት ስራው ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ከ15 አመት በላይ አገልግሎት ላይ ሳይውሉ፣ ተበላሽተው ሳይወገዱ ተገኝተዋል፡፡

ድርጅቱ ለ21 ዳፍ አውቶብሶች ከግብፅ ከ14.2 ሚሊዮን ብር መለዋወጫ ተገዝቷል ተብሎ ቢገጠምላቸውም ሞተሩ ግን ከ6 ወር በላይ ሳይሰራ የተባላሸ መሆኑም ተደርሶበታል፡፡

የካቲት 24 ቀን 2009 በአንበሳ ድርጅት የመካኒሳ ዴፖ በሚገኘው የጥገና ጋራዥ ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ለወደሙ አውቶብሶች ዋስትና ባለመግባቱ ከ8 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደርሶበታል ተብሏል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ዋጋቸው በትክክል የማይታወቅ ብዛት ያላቸው የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ክፍት በሆኑ ኮንቴይነሮች እና በሜዳ ላይ ለጥበቃ በማይመች ሁኔታ በየካ ዴፖ ተቀምጦ መገታቸውንም ታውቋል፡፡

ምንጭ፡- ሸገር ሬድዮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here