ሰሞኑን የተወሰኑ ወገኖች እኔን በተመለከተ የለቀቁትን ቪዲዮ የተመለከታችሁ ወዳጆቼ ስለ እኔ በማሰብ ጠይቃችሁኛል፡፡

ይህን መሰሉን ስም ማጥፋት ላለፉት ሃያ ዓመታት ለምጄዋለሁ፡፡

ሰው ቀና ያለ ሲመስላቸው አናትን መኮርኮም ልማዳቸው ያደረጉ ሰዎች ገና ብዙ ያሳዩናል፡፡

የኦሮምኛ መዝሙር እንዲኖር፣ በኦሮምኛ ስብከት እንዲሰጥ፣ በኦሮምኛ የሚያስተምሩ መምህራን እንዲሠለጥኑ ገና በወጣትነታችን

የዛሬ 20 ዓመት በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ከታገሉት ወንድሞችና እኅቶች መካከል አንዱ ስለሆንኩ ለዚህ ዓይነቱ ክስ መልስ መስጠት አይጠበቅብኝም፡፡

ከእኔ በላይ የምዕራብ ወለጋዎቹ ጊምቢ፣ ቂልጡ ካራ፣ ነጆና መንዲ ምስክሮች ናቸውና፡፡

ይህንን ቪዲዮ እንኳን ከሁሉም ሰው ዘግይቼ ያየሁት በጂጂጋ በደረሰው መከራና ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው በመጡት ኦሮሞዎች ጉዳይ ከሚመለከታቸው ጋር ሥራ ላይ ስለነበርኩ ነው፡፡

ቪዲዮዎችን ቆርጦ በመቀጠል ለውጥ አመጣለሁ ብሎ የሚያስብ ካለ ይቀጥል፡፡

እኔ ያስተማርኩት ግን አንድ ክህደቱን ደብቆ ከድሬዳዋ እስከ አሜሪካ በኦሮሞ ሕዝብ ስም እየነገደ ስለሚገኝ ሰው ጉዳይ ብቻ ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ ድሬዳዋዎች በሚገባ ጉዳዩን ያውቁታል፡፡ ዝርዝር መረጃውም አለኝ፡፤

የተውኩት እንክርዳዱ ሲነቀል ስንዴው አብሮ እንዳይጎዳ በሚል ነው፡፡

ከዚያ ውጭ ሰዎቹ ባሰቡት መጠን ለመውረድ ያለሁበት የሰብእና ልክ አይፈቅድልኝም፡፡

በነገሩ ውስጥ ብዙ ገብቼ ስነታረክ የማልውለው ነፍሰ ሔር ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ

‹ሥራህን ሥራ፤ አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል፤

የሰይጣንንም ውሻዎች ለመውገር አትቁም፤ ጥንቸሎቹን በማባረር ጊዜህን አታጥፋ፤

ሥራህን ሥራ› ያሉትን እንደ ሕይወት መመሪያ ስለምመራበት ነው፡፡

ይህንም የጻፍኩት የወንድሞቼን ምክር መቀበሌን ለመግለጥ ያህል ነው፡፡

የሚጮኸውን ውሻ ሁሉ አፍ ለማዘጋት ጊዜያችንን የምናባክን ከሆነ ሀገርንና ወገንን ለማገልገል የሚተርፍ ጊዜ አይኖረንም፡፡

ወርቅን አቧራ ስላለበስከው ዋጋውን አትቀንሰውም፡፡

ለጊዜው መልኩን ታሳስተው ይሆናል እንጂ፡፡ ማንጠሪያው ሲመጣ ሁሉም ይታወቃል፡፡

Tibebu Sime

What is wrong with singing gospel songs in Afaan Oromo in a church? Deacon Daniel Kibret must unconditionally apologize to the people Oromo for this offensive remark and immediately resign from his position as a director of the National Archives and Library of Ethiopia because racists shouldn’t be allowed to hold any position in the government. *** This kind of hateful remark can be a recipe to establishing Oromia Orthodox Church. I think it should be considered.

Posted by Tibebu Sime on Tuesday, August 14, 2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here