አንዳንዴ ልብ ያሸንፋል!

ሌላ ግዜ አእምሮ ይረታል!

እስቲ አንድ ተረት ልንገራችሁ፦በአንድ መንደር ውስጥ ሁለት ለማኞች ይኖራሉ―አንደኛው እውር ነው፣ሁለተኛው አንካሳ።

እነኚህ ለማኞች ለተመሳሳይ ስራ ስለሚፎካከሩ እርስ በእርስ በጣም ይጠላላሉ።

ታዲያ አንድ ቀን በመንደሩ እሳት ይነሳል። አንካሳው እሳቱን ቢያየውም መሮጥ አይችልም።

እውሩ መሮጥ ቢችልም እሳቱን ማየት ስለማይችል ወደየት መሮጥ እንዳለበት አያውቅም።

እነዚህ ሁለት ጠላቶች አጉል ጠላትነታቸውን ወደጎን አድርገው በህብረት ለመስራት ተስማሙ። አንካሳው እየመራ እውሩ እየሮጠ ከእሳቱ አመለጡ።

እነዚህ ሁለት ለማኞች ልብና አእምሮ ናቸው። መንፈሳችን በማያቋርጥ የምኞት እሳት ይቃጠላል።

አእምሮአችን ለብቻው እውር ነው። ወደየት መሄድ እንዳለበት መወሰን አይችልም።

አእምሮ በልምድ የዳበረ እውቀት አለው ይሁን እንጂ የወደፊቱን መመልከት አይችልም።

ልብ መመልከት ማስተዋል ይችላል ነገር ግን ይህንን ያስተዋለውን ነገር አእምሮ እንዲረዳለት ይፈልጋል። የሁለቱ ቅንጅት እንዲህ ቀላል ነው።

መፎካከሩን ትተው ለአንድ አላማ ይሰለፋሉ። አሸናፊ እና ተሸናፊ የለም።

ሁለቱም ለአንድ አላማ ተሰልፈው ሁለቱም አሸናፊ ይሆናሉ። ልብና አእምሮ ጠላቶች አይደሉም።

ሁለቱ ሲረዳዱ ታላቅ ነገርን ማከናወን ይችላሉ።

አንዳንዴ አእምሮአችን አንድ ነገር፤ ልባችን ደግሞ ሌላ ነገር ይነግሩናል። ልብ መመልከት ስለሚችል በመጀመሪያ እሱን እናዳምጣለን።

ነገር ግን ልብ ያሳየንን መንገድ ለመከተል አእምሮአችንን እንጠቀማለን። ይኸው ነው!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here